የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የ2008 በጀት ዓመት አፈፃፀም ውጤታማ እንደ ነበር ተገለፀ፡፡

Body: 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ከተለያዩ የመንግስትና የግል የሚዲያ ተቋማት ጋር ባዘጋጀው የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ድርጅቱ የ2008 በጀት ዓመት እቅዱን 92.2% በማጠናቀቅ የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን አሳውቋል፡፡.
ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ 4,966,265 ቶን ገቢ እቃዎችን በራሱና በኪራይ መርከቦች ወደ ሀገሪቱ ያስገባ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 57.5% የኮንቴነር ጭነት 16.4% ብረት እና 1.7% ደግሞ የተሽከርካሪ ጭነቶች እነደሆኑ ተገልጿል፡፡. .

ድርጀቱ ወደ ደረቅ ወደቦችና ወደ ቦንድድ መጋዘኖች ለሚገቡ ለ 175,672 ኮንቴነሮች እና ለ 14,736 መኪኖች የጭነት ማስተላለፍ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ለ 274,043 ቶን ወጪ ዕቃዎች በዩኒ ሞዳል የትራንስፖርት ስልት የጭነት ማስተላለፍ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ድርጅቱ በሚያስተዳድራቸው ደረቅ ወደቦችም 162,047 TEU ኮንቴነሮች እና 13,224 ተሽከርካሪዎች መስተናገዳቸውን በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሰጣቸው የባህር ትራንስፖርት የጭነት ማስተላለፍ እና የወደብና ተርሚናል አገልግሎቶች በአጠቃላይ 16.586 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 15.129 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ 1.29 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል፡፡.

በድርጅቱ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ከተሰጠው ገለፃ ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማሳደግና የካፒታል ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ባለፈው አመት ከታየው አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተጠናክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

File: