እንኳን ደስ አላችሁ!!

Body: 

ለውድ ደንበኞቻችንና የድርጅታችን ሠራተኞች በሙሉ
የድርጅታችን የተፈቀደ ካፒታል ከብር 3.76 ቢሊዮን ወደ ብር 20 ቢሊዮን ከፍ እንዲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2ዐዐ8 ዓ/ም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የድርጅቱ ካፒታል እንዲያድግ መፈቀዱ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን የድርጅታችንን አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ የሚያደርገውና አገልግሎት አሰጣጡንም በከፍተኛ ደረጃ እንዲሻሻል የሚያደርግ በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችንና መላው የድርጅታችን ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡