መልካም ዜና ለክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ

Body: 

መልካም ዜና ለክቡራን ደንበኞቻችን በሙሉ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በሚሰራባቸው ወደቦች ያለውን ወቅታዊ የገበያ ሁኔታ መሰረት በማድረግ በባህር ትራንስፖርት ማጓጓዣ ዋጋዎች ላይ ቅናሽ ማድረጉን በደስታ ይገልፃል፡፡
በዚህም መሰረት፣

  •  ለባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች ከ303 መነሻ ወደቦች - በአማካይ 19% ቅናሽ
  •  ለባለ 40 ጫማ ኮንቴነርች ከ303 መነሻ ወደቦች - በአማካይ 22.7% ቅናሽ
  •  ለተሽከርካሪ 1 ሮሮ ዕቃ ከ48 መነሻ ወደቦች - በአማካይ 10.2% ቅናሽ
  •  ለግንባታ ብረታ ብረት በቶን ከ11መነሻ ወደቦች - ከ2-7 የአሜሪካን ዶላር
  •  ለጥቅል ዕቃዎች በቶን ከ6 መነሻ ወደቦች - ከ5-15 የአሜሪካን ዶላር

ቅናሽ ያደረግን መሆኑን እየገለፅን፣ ቅናሹ እ.ኤ.አ ከሚያዚያ 01, 2016 ጀምሮ ለቀጣይ 6 ወራት መሆኑን ተረድተው ደንበኞች እንዲጠቀሙ ይጋብዛል፡፡
በተጨማሪም ድርጅቱ የኮንቴይነር የመጠቀሚያ የዕፎይታ ጊዜ ከ15 እስከ 30 ቀናት መሆኑን እና የኮንቴይነር ዲፖዚት መጠኑም አሁን ካለው የገበያ ዋጋ 30% ብቻ በመያዝ እንደሚያስተናግድና ለአንድ ወር ያላነሰ የፍሬይት ዋጋ በዱቤ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
“አገልግሎታችን በዋጋ፣ በጥራትና በጊዜ ተወዳዳሪ እንዲሆን ምንጊዜም እንተጋለን፡፡”
ለጥረትዎ ዕሴት እንጨምራለን!