የድርጅቱ የሥራ መሪዎች ጉባዔ ተካሄደ

Body: 

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሥራ መሪዎች ጉባዔ በመቐለ ከተማ ከመጋቢት 01-02/2010 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ በጉባዔው ላይ የዋናው መ/ቤት እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ስራ መሪዎች የተገኙ ሲሆን የድርጅቱን የ2010 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ስድስት ወራት የመደበኛ ሥራ፣ የካፒታል ፕሮጀክት፣ የለውጥ እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወራት መከናወን ያለባቸው የድርጅቱ የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚመለከት በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ከውይይቱ በኋላም የመቐለ ወደብና ተርሚናልን፣ የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክንና የሰማዕታት ሐውልቱን ያካተተ ጉብኝት በተሳታዎች ተካሂዷል፡፡

File: 
File1: