ድርጅቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ደንበኞች እውቅና ሰጠ

Body: 

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ደንበኞች ማለትም ለመንግስትና ለግል አስመጭና ላኪዎች እንዲሁም ለአምራችና ኤክስፖርተሮች የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ የእውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ሰጥተዋል፡፡ የእውቅና መስጠት ፕሮግራሙ የተካሄደው የድርጅቱ የ2010 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ጊዜ በጋራ ለሚከናወኑ ስራዎች ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አስመልክቶ ታህሳስ 5/2010 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በጋራ በተወያዩበት ዕለት ነው፡፡


File: 
File1: 
File2: