ማስታወቂያ

Body: 


የኮንቴይነር ተመላሽ ክፍያ ለመውሰድ ደንበኞች ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ማሳወቅን ይመለከታል
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ደንበኞች ዕቃዎችን ወደ ውጪ ሲልኩም ሆነ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ የኮንቴይነር ማስያዣ ክፍያ ቀድመው ማስያዝ እንዳለባቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዕቃዎችን ከተረከቡ በኋላ ያስያዙትን ተመላሽ ገንዘብ ለመውሰድ እና ኮንቴይነሩን ከራሳቸው ተጠያቂነት መመለሳቸውን ለማወራረድ ወደ ድርጅቱ ሲመጡ ማቅረብ ያለባቸውን ሰነዶች አንዳንድ ደንበኞች ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ጠፋብን በሚል ምክንያት ባለማቅረባቸው ክፍያ መፈጸም አልተቻለም፡፡ ስለሆነም ደንበኞች በሰነድ አያያዝ ላይ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን የኮንቴይነር ተመላሽ ክፍያ ለመውሰድ ማሟላት ያለባችሁ ሰነዶች፡-
• Equipment Interchange Report (EIR) Full Out and Empty In ኦርጅናል ሰነድ
• Cash Receipt Voucher ኦርጅናል ሰነድ
• Bill of Lading ኮፒ ሰነድ
በማቅረብ የምትስተናገዱ መሆኑን እየገለጽን ከላይ የተዘረዘሩ ሰነዶችን አሟልቶ ለማይመጣ ደንበኛ ክፍያ የማንፈጽም መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ለጥረትዎ እሴት እንጨምራለን!
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት

File: