የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በድምቀት ተከበረ

Body: 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የዋና ጽ/ቤት ስራ መሪዎችና የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት "ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ የተከበረውን የሰንደቅ ዓላማ በዓል ቀን በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት በድምቀት ተከበረ፡፡

በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ደንቡ እንደገለጹት ሰንደቅ ዓላማችን የነጻነታችንና የሉዓላዊነታችን መገለጫ፣ የሕብረ - ብሔራዊነታችንና እኩልነታችን ተምሳሌት፣ ለሠላም፣ ለልማትና ለዴሞክራሲ ሲሉ ለተሰውና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖቻችን ህያው መታሰቢያ ዓርማ ነው ብለዋል፡፡ የአሁኑ ትውልድም የሰንደቅ ዓላማ በዓልን ስናከብር የቀደሙት አባቶቻችን የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ያስረከቡንን ሀገር በተሰማራንበት ሙያ መስክ የበኩላችን በመወጣት ድህነትንና ኃላቀርነትን ለማስወገድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባናል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ የመስቀልና ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር የዕለቱ ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል፡፡

File: 
File1: