የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

Body: 

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ስለ ድርጅቱ የ2009 በጀት ዓመት አፈጻጻም፣ የ2010 ዕቅድና አጠቃላይ የድርጅቱን ወቅታዊ ጉዳይ በሚመለከት ለሃገር ውስጥ የግልና የመንግስት መገናኛ ብዙኃን መስከረም 13/2010 ዓ/ም በጽ/ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንደተመለከተው የድርጅቱን ዋና ዋና የመደበኛ ሥራዎች የ2009 በጀት አፈጻጸም በሚመለከት ሲገልጹ የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም በባሕር ላይ 5,319,286 ቶን ኮንቴይነር፣ ተሽከርካሪ፣ ጥቅል ዕቃ፣ ብረት እና ብትን ገቢ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ታቅዶ 4,538,722 ቶን ያጓጓዘ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 85.3% መፈጸም ሲቻል የድርጅቱ መርከቦች አፈጻጸም ግን ዝቅተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በጭነት ማስተላለፍ አገልግሎት ዘርፍ በባሕር ከተጓጓዘው ውስጥ በመልቲ ሞዳል ከጅቡቲ ወደ መሃል አገር 183,942 TEU ኮንቴይነር እና 21,961 ተሽከርካሪዎችን ለማጓጓዝ ታቅዶ 179,170 TEU ኮንቴይነር በማጓጓዝ የዕቅዱን 97% ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የትራንዚት ጊዜን 95% ለማድረስ በዕቅድ ከተቀመጠው 91% መፈጸም መቻሉን በጋዜጣዊ መግለጫቸው አመላክተዋል፡፡
የወደብና ተርሚናል አገልግሎትን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ 174,744 TEU ገቢ ኮንቴይነር በወደቦች ለማስተናገድ ታቅዶ 169,241 ኮንቴይነር በማስተናገድ የእቅዱን 97% መፈጸም ሲቻል ወጪ ኮንቴይነር ደግሞ 169,131 TEU ለማስተናገድ ታቅዶ 171,346 ኮንቴይነር በማስተናገድ የእቅዱን 101% ማሳካቱን አብራርተዋል፡፡


በአጠቃላይ ድርጅቱ የባሕር ትራንስፖርት፣ ጭነት ማስተላለፍ እና የወደብ አገልግሎት በመስጠት በበጀት ዓመቱ 16.54 ቢሊዮን ብር በማስገባት የዕቅዱን 86% ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የ2010 በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅድ አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ከቀረበው ሪፖርት እና ዕቅድ በመነሳት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና አስተያቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

File: 
File1: