ማስታወቂያ

Body: 

ያለ ባንክ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ህጋዊነትን ይመለከታል
ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የንግድ ዕቃዎች በባንክ ፈቃድ ወይም ህጉ ለሚፈቅድላቸው በፍራንኮቫሉታ አማካኝነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ሆኖም አንዳንድ ደንበኞች በስማቸው ምንም አይነት የባንክ ፈቃድ ሳይኖራቸው "ላኪዎች ተሳስተው በሰሜ የላኩት ነው" በሚል ሰበብ ዕቃዎች በመልቲሞዳል ተጓጉዘው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ የጭነት ሰነድ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ ያታያሉ
አንድ አስመጪ በስሙ የባንክ ፈቃድ ሳይኖረው ዕቃን አገር ውስጥ ማስገባት በአገራችን የንግድ ስርዓትና በብሄራዊ ባንክ መመሪያ የተከለከለ ስለሆነ፣ በዚህ መልክ የገባ ዕቃ የጭነት ሰነድ ላይ የስም ማስተካከያ ማድረግ የማይቻል መሆኑን እያስታወቅን የባንክ ፈቃድ ሳይኖረው በመርከብ ላይ ዕቃ ያስጫነ ደንበኛ ቢኖር ጥያቄው መቅረብ ያለበት ዕቃው በትራንዚት ላይ እያለ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት