የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የድርጅቱን ሁለገብ ዘመናዊ ህንጻ ግንባታ ጎበኙ

Body: 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት እያስገነባ ያለውን ሁለገብ ዘመናዊና ግዙፍ ህንጻ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የድርጅቱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንዲሁም የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የኢባትሎአድ ከፍተኛ አመራር አባላት በተገኙበት ሰኔ 29/2009 ዓ/ም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የህንጻውን ግንባታ እያከናወነ ያለው የተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን ድርጅት የህንጻው ፕሮጀክት ማኔጀር ኢንጂነር አበረ ንጉሴ በበኩላቸው ህንጻውን በውለታው (በኮንትራቱ) መሰረት ለማጠናቀቅ እንዳልተቻለ ገልጸው አብዛኛዎቹ የማጠናቀቂያ እቃዎች ከውጪ ሀገር ተገዝተው የሚገቡ መሆናቸው እና ግዥ ለመፈጸም የውጪ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ የህንጻውን ግንባታ በታሰበው ፍጥነት ለማጠናቀቅ አልተቻለም ብለዋል፡፡
አሁን ግን የውጪ ምንዛሪ እጥረቱ እንደተቀረፈ እና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በፍጥነት በማስገባት የህንጻውን ግንባታ ሙሉ ለሙሉ አጠናቀው ለድርጅቱ እንደሚያስረክቡ አሰታውቀዋል፡፡

ህንጻው በ3000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ፣ 74 ሜትር ከፍታ ያለው፣ ባለ 20 ፎቅ እና ሁለት የምድር ቤት ተሽከርካሪ ማቆሚያ ያለው እንዲሁም ከማሪታይም ህንጻ ጋር በግራውንድና 1ኛ ፎቅ በኩል የሚያገናኝ ድልድይ ያለው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

File: 
File1: